That sounds incredible! Music has a way of bringing people together for a meaningful cause, especially when it supports something as significant as acquiring a Church building. Blen Markos's song dedication program seems like it was a beautiful way to contribute to the community and the Church's goals. May God bless her and her family.
Research Center
በካናዳ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ኦከቶበር 10 ቀን 2023 ባደረገው የመሪዎች ስብሳ በየደረጃው አዲስ የአመራር አባላትን መርጧል፡፡ በሕብረቱ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 9; መሠረት በየ3 አመቱ ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ፣ 3 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴና ለምስራቅና ምዕራብ ካናዳ አብያተ ክርስቲያናት ለእያንዳንዳቸው 3 መሪዎችን ይመርጣል፡፡
በዚህም መሰረት በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀጽ 10;2 ለ2 ተከታታይ ስራ ዘመን ባገለገሉት በፓስተር መልኬ ነጋሽ ምትክ ፓስተር ደረጀ ኃይለየሱስን የሕብረቱ ሰብሳቢ አድርጎ መርጧል፡፡ ፓስተር ተረፈ ሰረቀ የሕብረቱ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ሲመረጡ
በተጨማሪም ለሕብረቱ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት
ፓስተር ቻላቸው እሽቱ
ፓስተር ዶ/ር ኤፍሬም ላዕከ ማርያም
ፓስተር አማረ ተክሉ
- ለምስራቅ ካናዳ አብያተ ክርስቲያናት መሪነት
ፓስተር መስፍን ብርሃኑ
ፓስተር ኢያሱ ተስፋዬ
ፓስተር ዶ/ር ግርማ በቀለ
- ለምዕራብ ካናዳ አብያተ ክርስቲያናት መሪነት
ፓስተር ወርቅነህ ሞገሴ
ፓስተር ዱባ ገልገሌ
ፓስተር ዶ/ር ወርቁ መኮንን ሆነው ተመርጠዋል።
ለአዲሶቹ ተመራጮች መልካም የስራ ዘመን እየተመኘን በቅንነት አገልገለው ኃላፊነታቸውን በመወጣት ለቀጣይ መሪዎች ላስረከቡት መሪዎቻችን ደግሞ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

ሴፕቴምበር 16 ቀን 2023 ዓመተ ምሕረት በተደረገው የደመቀ ስነ ስርዓት ላይ ቤተክርስቲያኗ በውስጧ እያገለገሉ ከነበሩ ቅዱሳን መካከል ወንድም ጥሩ ሰው ወልደየስንና ወንድም በፈቃዱ በመጋቢነት የሾመች ሲሆን የአገልግሎት ምደባቸውንም አሳውቃለች፡፡ በዕለቱ በተደረገው መንፈሳዊ የሹመት ስነ ስርዓት የቤተክርስቲያኗ ምዕመናን ፣ ከካናዳ የተለያዩ ከተሞች የመጡ በርካታ ቅዱሳን ፣ የኢትዮጵያና የኤርትራ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት መጋቢዎች ፣ ዘማሪዎችና አገልጋዮች ተገኝተዋል፡፡
በዕለቱ የመጋቢዎችን ቃል የመግባትና የሹመት ስርዓት ያስፈጸሙት የቤተክርስቲያኗ ዋና መጋቢ ፓስተር መስፍን ብርሃኑ ሲሆኑ ለተሿሚዎቹ የተዘጋጀውን የምስክር ወረቀት የሰጡት ደግሞ ፓስተር ዮሐንስ ተፈራ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ከርሰቲያናት ሕብረት ዋና ጸሐፊ ናቸው፡፡
On September 16, 2023, Bethel Ethiopian Evangelical Church in Kitchener appointed two pastors among the saints who were serving in the church for a long time with a specified responsibility. In the Pastoral ordination ceremony held that day , the parishioners of the Church, Many Pastors, Gospel singers and ministers of the evangelical churches of Ethiopia and Eritrea were present.
Pastor Mesfen Berhanu, the Lead Pastor of the church, performed the Ordination process of the appointment ceremony of the pastors, followed by Pastor Yohannes Teffera, the general secretary of the Ethiopian Evangelical Churches Fellowship in Canada who distributed the certificate to the appointees.
- በካናዳ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ዋና ጸሐፊ ፓስተር ዮሐንስ ተፈራ በጉባኤ ተጸልዮላቸው ኃላፊነታቸውን ተረከቡ፡፡Pastor Yohannes Tefera, General Secretary of the Union of Ethiopian Evangelical Churches in Canada, assumed his duties.
- የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት በካናዳ 30ኛ ዓመታዊ የመሪዎች ስብሰባንና የሕብረቱን ዋና ጸሐፊ አገልግሎት ማስጀመር አስመልክቶ የተዘጋጀ ልዩ ኮንፈረንስ
- የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት በካናዳ 30ኛ ዓመታዊ የመሪዎች ስብሰባ Ethiopian Evangelical Churches Fellowship In Canada 30th Annual Leadership Meeting Program September 18 - 24 , 2023
- የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት በካናዳ ዋና ጸሐፊ ሾመ