በካናዳ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት አዲስ የአመራር አባላትን መረጠ፡፡
በካናዳ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ኦከቶበር 10 ቀን 2023 ባደረገው የመሪዎች ስብሳ በየደረጃው አዲስ የአመራር አባላትን መርጧል፡፡ በሕብረቱ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 9; መሠረት በየ3 አመቱ ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ፣ 3 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴና ለምስራቅና ምዕራብ ካናዳ አብያተ ክርስቲያናት ለእያንዳንዳቸው 3 መሪዎችን ይመርጣል፡፡
በዚህም መሰረት በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀጽ 10;2 ለ2 ተከታታይ ስራ ዘመን ባገለገሉት በፓስተር መልኬ ነጋሽ ምትክ ፓስተር ደረጀ ኃይለየሱስን የሕብረቱ ሰብሳቢ አድርጎ መርጧል፡፡ ፓስተር ተረፈ ሰረቀ የሕብረቱ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ሲመረጡ
በተጨማሪም ለሕብረቱ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት
ፓስተር ቻላቸው እሽቱ
ፓስተር ዶ/ር ኤፍሬም ላዕከ ማርያም
ፓስተር አማረ ተክሉ
- ለምስራቅ ካናዳ አብያተ ክርስቲያናት መሪነት
ፓስተር መስፍን ብርሃኑ
ፓስተር ኢያሱ ተስፋዬ
ፓስተር ዶ/ር ግርማ በቀለ
- ለምዕራብ ካናዳ አብያተ ክርስቲያናት መሪነት
ፓስተር ወርቅነህ ሞገሴ
ፓስተር ዱባ ገልገሌ
ፓስተር ዶ/ር ወርቁ መኮንን ሆነው ተመርጠዋል።
ለአዲሶቹ ተመራጮች መልካም የስራ ዘመን እየተመኘን በቅንነት አገልገለው ኃላፊነታቸውን በመወጣት ለቀጣይ መሪዎች ላስረከቡት መሪዎቻችን ደግሞ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡