የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት በካናዳ 30ኛ ዓመታዊ የመሪዎች ስብሰባ Ethiopian Evangelical Churches Fellowship In Canada 30th Annual Leadership Meeting Program September 18 - 24 , 2023
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት በካናዳ 30ኛ ዓመታዊ የመሪዎች ስብሰባ የፊታችን ሰኞ ሴፕቴምበር 18 ቀን 2023 ዓመተ ምሕረት በቶሮንቶ ከተማ ይጀመራል፡፡
በዚህ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ በተለያዩ የካናዳ ከተሞች የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ወደ ቶሮንቶ ይመጣሉ፡፡ ስብሰባው ሰኞ ሴፕቴምበር 18 ቀን ተጀምሮ ዐርብ ሴፕቴምበር 22 እኩለ ቀን ላይ ይጠናቀቃል፡፡ ሕብረቱ ዓመታዊ ስብሰባው በሚስተናገድበት ከተማ ኮንፈረንስ በማድረግ የአምልኮና የምስጋና ጊዜ የሚያደርግ ሲሆን በዚህም መሰረት ዐርብ ምሽትአንድ ፕሮግራም ቅዳሜ ከሰዓት በኋላና ምሽት 2 ፕሮግራሞች ይደረጋሉ፡፡
የዘንድሮውን ስብሰባ የተለዬ የሚያደርገው ለዓመታት የሕብረቱን ስራ በሙሉ ጊዜ የሚያስተባብር አገልጋይ ጌታ እንዲሰጥ ሲጸለይበት የነበረው የጸሎት ጥያቄ የተመለሰበት መሆኑ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ከተለያዩ ከተሞች የተሰባሰቡት የሕብረቱ መሪዎች ከቶርንቶ ቅዱሳን ጋር በመሆን ለፓስተር ዮሐንስ ተፈራና ለባለቤቱ በመጸለይ ‹ዕጅ በመጫን ኃላፊነቱን በኦፊሲየል ያስጀምራሉ፡፡ ይህም የጸሎት ፕሮግራም ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ሴፕቴምበር 24 ቀን ዕሁድ ጧት በቶሮንቶ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ጉባኤ ላይ ይከናወናል፡፡
በዚሁ 30ኛ ዓመታዊ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ለመሪዎች ወቅታዊ ትምሕርት እንዲያቀርቡ የተጋበዙት ፓስተር በድሉ ይርጋ በዳላስ ቴክሳስ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ባፕቲስት ቤተክርስቲያን ዋና መጋቢ ናቸው፡፡