News and Updates

አቶ ሊበን ገብረ ሚካኤል እንኳን ደስ አለዎት ! Congratulations Ato/Mr Liben Gebremikael

አቶ ሊበን ገብረ ሚካኤል እንኳን ደስ አለዎት ! Congratulations Ato/Mr Liben Gebremikael

https://canadianimmigrant.ca/canadas-top-25-immigrants/top-25-canadian-immigrant-awards-2025/liben-gebremikael

Gebremikael, who recently received the King Charles III Coronation Medal, adds “I truly believe that if we can all come together and work toward a common goal, we can make a difference.”

የሊበን መንገድ/ Liben Way

በቶሮንቶ ከተማ ውስጥ በማልቨርን ውስጥ “Liben Way” ተብሎ የሚታወቅ መንገድ አለ። ይህ መንገድ በ2022 ዓ.ም በአቶ ሊበን ስም የተሰየመ ሲሆን  ይህም የተደረገው የTAIBU   ጤና ማዕከል መጀመሪያ ዋና  ዳይሬክተርና   ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሊበን ገብረሚካኤልን ለማክበር ነው። አቶ ሊበን ገብረሚካኤል ባለፉት 17 ዓመታት TAIBUን ለጥቁሩ ማሕበረሰብ  የጤናና    የልማት አካል አንዲሆን   በትጋት  በመስራት ከፍተኛ ዋጋ የከፈሉ  ናቸው።

አቶ ሊበን ገብረሚካኤል ከ20 በላይ በኅበረተስቡ ውስጥ አዲስ ተቋቋሚ የሆኑ  ድርጅቶችን — ማለትም አንደ  የGOOH እና Kidy Foundation Canadaን  የመሳሰሉትን ጨምሮ ከመነሻ እስከ መቋቋም ድረስ ባለው ሂደት ውስጥ   በመደገፍ እጅግ  ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡። ይህም  ከኦቲዝም እንክብካቤ ጀምሮ  ኢትዮጵያ ውስጥ አስከሚደረገው የትራፊክ አደጋን መከላከል የሚቻልበትን ግንዛቤና ድጋፍ አስከሚሰጠው ድርጅት ያሉትን  የሚያካትት ነው። አቶ ሊበን እንደሚሉት፦ “በመጀመሪያ ደረጃ የማህበረሰብ ድርጅቶች ራሳቸውን ችለው ሲቋቋሙና አስተዋጽዖ ሲያበረክቱ ሌሎችንም ለመደገፍ የሚችል አቅም ያላቸው አካላት ሆነው ሲገኙ ከማዬት የበለጠ ትልቅ ቦታ የምሰጠውና ሚያሰደስተኝ ነገር የለም ይላሉ፡፡