News and Updates

ለአቶ ሊበን ገብረሚካኤል ድምጽ እንስጥ። የመጨረሻው ድምጽ መስጫ ቀን ጁን 5 ስለሆነ አሁኑኑ ድምጽ ይስጡ።

ለአቶ ሊበን ገብረሚካኤል ድምጽ እንስጥ። የመጨረሻው  ድምጽ መስጫ ቀን ጁን 5 ስለሆነ አሁኑኑ ድምጽ ይስጡ።

በካናዳ ኢሚግራንት መካከል ጉልህ አስተዋጽዖ ላበረክቱ ዜጎች ከፍተኛ እውቅና ለሚያስገኘው ሽልማት  ውድድር አመታዊ የድምጽ መስጫ ውድድር በይፋ ጀምሯል። ተወዳዳሪዎቹ ወደ ካናዳ ከተለያዩ አገሮች የመጡና በሕዝባቸውና በካናዳ ታዋቂ ዜጎች ናቸው። 

አቶ ሊበን ገብረሚካኤል 25 የካናዳ የስደተኞች ተሸላሚዎች አንዱመሆን  75 እጩዎች ውስጥ አንዱ በመሆን ተመርጧል። በመቀጠልም  25 ከፍተኛ ድምጽ የሚያገኙት አሸናፊዎች ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ አቶ ሊበን በኅብረታችን የተደረገለትን ግብዣ በመቀበል በአዕምሮ ሕመም ዙሪያ በተዘጋጀው መርሐ ግብር ላይ ሙያዊ አስተጽዖ ማበርከቱ የሚታወስ ሲሆን በቶሮንቶ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ቀድሞ የሚገኝ ወንድማችን ነው፡፡

 https://canadianimmigrant.ca/contestants/gebremikael-liben   በመጫን አሁኑኑ ድምጽ ይስጡ ለሌሎችም ያስተላልፉ። 

ስለ አቶ ሊበን ገብረሚካኤል ለማወቅ

ሥራ                  ዋና አስፈፃሚ,  TAIBU የማህበረሰብ ጤና ማዕከል

ከተማ:                ቶሮንቶ

የትውልድ ሀገር፡    ኢትዮጵያ

አቶ ሊበን ገብረሚካኤል TAIBU የተሰኘ የማህበረሰብ ጤና ማእከል መስራችና  ዋና ዳይሬክተር ሲሀን እና የወቅቱ  ዋና ሥራ አስፈፃሚ ነው። ድርጅቱ ባለፉት 17 አመታት እያደገ ያለና  በታላቁ ቶሮንቶ አካባቢ ላሉ ጥቁር ህዝቦች፣ Scarborough ላሉ የፈረንሳይኛ ተናጋሪ ማህበረሰቦች እና ለሁሉም የማልቨርን ሰፈር ነዋሪዎች አዲስ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ፣ የጤና አጠባበቅና  የማህበረሰብ አቅም ግንባታ ፕሮግራሞችን ይሰጣል። በአቶ ሊበን ገብረሚካኤል አመራር TAIBU በመላው ካናዳ ውስጥ በጥቁር ጤና ውስጥ መሪ ሆኖ ይታወቃል። Inugural Scarborough Hero Award የጥቁር ጤና አሊያንስ ሽልማት በማህበረሰብ ተሳትፎ የላቀ ሽልማት፣ በጃማይካ ካናዳ ማህበር የላቀ ድርጅት ሽልማት እና Alliance for Healthier Communities የትራንስፎርሜሽን ለውጥ ሽልማትን ጨምሮ በርካታ ሽልማቶችን አግኝቷል።

አቶ ሊበን ገብረሚካኤል በተለያዩ ድርጆቶ የቦርዶች አመራር ውስጥ በመሳተፍ ማህበረሰቡን ያገለግላል። 2020-2023  Alliance for Healthier Communities የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሆኖም  አገልግሏል አቶ ሊበን  በአሁኑ ወቅት የኦንታርዮ የጤና መረጃ ምክር ቤት ሊቀመንበር እና የኦንታርዮ የመጀመሪያ ደረጃ እንክብካቤ ጥራት አማካሪ ኮሚቴ አባል ነው። አቶ ሊበን 20 በላይ የመሠረታዊ ማህበረሰብ ድርጅቶች በካናዳ በህጋዊ መንገድ እንዲመሰርቱ እና ለአዲስ መጤዎችና ስደተኞች እና የተለያዩ ማሕበረሰቦች  በጣም አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችን እና አገልግሎቶችን በመስጠት GOOH በኦቲዝም እና አረጋውያን የሚኖሩ ልጆች ያሏቸውን ወላጆች የሚረዳ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅትን በንቃት የመደገፍ አገልግሎትን በማበርከት ላይ ይገኛል። 

በኢትዮጵያ ያለውን አስደንጋጭ የመንገድ ትራፊክ አደጋ የሚፈታ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ግለሰቦች እና ቤተሰቦች መከላከል እና ጉዳትን ያማከለ እንክብካቤን የሚያገኝ ኪዲ ፋውንዴሽን ካናዳ የተሰኘ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት እንዲቋቋም አስተዋጽዖ አበርክቷል፡፡አቶ ሊበን  Alliance for Healthier Communities እና በፕላኔት አፍሪካ ግሩፕ የልማት ሽልማትን እንዲሁም የታዳጊ መሪዎች ሽልማትን ጨምሮ በርካታ ሽልማቶችን አግኝቷል። እ.ኤ.አ. በ2022፣ በኮቪድ-19   ወረርሽኝ ወቅት ለማህበረሰቡ ላበረከተው አስተዋፅዖ በማልቨርን የሚገኝ የግል ጎዳና በስሙ - “LIBEN WAY” ተብሎ ተሰይሞለታል።  እ.ኤ.አ. በ 2025 ፣ ለማህበረሰቡ ላደረገው አስተዋፅዖ የንጉሥ ቻርለስ III የንግስ በዓል መታሰቢያ ሜዳሊያን ተሸልሟል። አቶ ሊበን ገብረሚካኤል የሁለት ሴት ልጆች አባትና የአንድ ልጅ አያት ነው።

ማሳሰቢያ
አቶ ሊበን ገብረሚካኤልን አንተ በማለት ለማቅረብ የተደፈረው ቀለል ባለ ሰብዕና ከሕዝብ ጋር ባላቸው መግባባትና ቤተሰባዊ አቀራረብ ምክንያት መሆኑን ለማሳወቅ አንወዳለን፡፡