የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት በካናዳ

የካናዳ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያን ሕብረት በሐምሌ 1993 በካልጋሪ አልብርታ ተመስርቷል ፡ በወቅቱ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን አስተባባሪ ፓስተር ሲሳይ ቶይ እና በቫንኩቨ ር የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ፓስተር ከበደ ደጉ የቤተክርስቲያን መሪዎችን የጅማሬ በስብሰባዎች ጥሪ አድርገዋል።

ይህ ሕብረት ዛሬ ወዳለንበት ደርጃ እንዲደርስ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል ፤ ስለአደርጉት ጥረት ሁሉ ልናመሰግናቸው እንፈልጋለን። ይህ ሕብረት ከተጀምረ ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያን ወንጌላዊ  አብያተክርስቲያን ሕብረት መሪዎች በየሶስት ዓመታት ይመርጣሉ። ብዙ ፓስተሮች  አንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆነ የአገልግሎት ዘመን መሪ ሆነው አገልግለዋል፤ ለእነዚህ ግልጋሎት ወንድሞችን ሁሉ ሰለአገልግሎታቸው ሙሉ ምስጋናችንን ለመግለጽ እንወዳለን።  በነዚህ ዓመታት ሁሉ ከጌታ ቃልን ስንቀበል በአካባቢያችን  ያሉ አብያተክርስቲያኖችን በሁሉም የእኛ እንቅስቃሴዎች ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማድረስ ፍላጎታችን ነው፤  ይህም የጌታን ስራ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማድረስ ነው።.

መጋቢዎችን  የቤተክርስቲያን መሪዎች ሽማግሌዎች እና በአብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ውስጥ ያለን ሁላችን የቤተክርስቲያን አባሎች እንዋደድ አብረን እንስራ ፤ ጊዜያችንን እና የገንዘብ ድጋፍን ለጌታ ስራ በማደረግና እርስ በራስ እንደ እውነተኛ ወንድሞች እና እህቶች እንከባበር::

 

  • ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኃጢአተኛው እና ለኃጢአተኛ የሰው ዘር በመስቀል ላይ ለመሞት እና ለእኛ ያለውን ፍቅር ለማሳየት ወደዚህ ዓለም መጣ.

"በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።" (ዮሐ 3:16).

 "እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።" (ኢሳ 53:5)